top of page
Search

የማቴዎስ ወንጌል የምንባብ ማስታወሻ፦ ምዕራፍ 8

Updated: May 1, 2024

በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 8 ስናነብ እንደምናገኘው ጌታ ከተራራው ከወረደ በኋላ የአገልግሎቱን ቀጣይ ምዕራፍ የጀመረው ለምፃሙን በማንፃት፣ብላቴናውን ከሽባነት በመፈወስ፣በንዳድ የታመመችውን በማዳን፣ ከባሕር ማዕበል በመታደግና ከአጋንንቶች እስራት ነፃ በማውጣት ነው። በዚህ ምንባብ ክፍል እጅግ አስደናቂው ክንውንና የምዕራፉ ፈርጥ ሀሳብ ያለው በጌታ ኢየሱስና በመቶ አለቃው መካከል በተደረገው ንግግር ውስጥ ነው።አረማዊ በመሆኑና በአይሁድ በመናቁ መቶ አለቃውን መጥቼ እፈውሰዋለሁ ባለው ግዜ ‘ለእኔ ይህ አይገባኝም እኔ በስሬ ያሉትን አድርጉ ብዬ ሳዝ እንደሚያደርጉ አንተ ደግሞ በፈውስ ላይ የማዘዝ ስልጣን አለህ ቃል ተናገር፣ ብላቴናዬ ይፈወሳል’ አለ።ጌታም በእምነቱ ተደንቆ “በእስራኤል ይህን መሰል ትልቅ እምነት አላየሁም ሂድ እንዳመንህ ይሁንልህ” አለው። በዚህ ምክንያት ጌታ ብዙዎች አይሁድ ያልሆኑ መጥተው የእግዚአብሔርን መንግሥት ሲወርሱ በስጋ የአብርሐም ልጆች የተባሉት መሲሁን አንቀበልም በማለታቸው ወደ አስፈሪ ጨለማ የመጣላቸውን ትንቢት ይናገራል።

 
 
 

Comments


Commenting on this post isn't available anymore. Contact the site owner for more info.

Living Gospel Church

525 William Ave, Winnipeg, Manitoba, Canada. R3A 0J7

Tel:- (204) 775-7818

Email:- lgcwinnipeg@gmail.com

© 2024 Living Gospel Church All Rights Reserved | Privacy & Legal

SUBSCRIBE FOR EMAILS

Thanks for submitting!

  • Youtube
  • Facebook
bottom of page